Tuesday, June 16, 2015

ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርጫፍ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ ተብሎው በኢህአዴግ ባለስልጣናት መነገራቸው ተገለጸ።



በደረሰን መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣን በሆነው በአዲሱ ለገሰ በተደረገው የስብሰባ መሪነት አብዛኛው የአቢሲያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ፤ ከመንግስት ጋር ያላችሁን ችግር በውይይት እንፋታው ብሎ በከፈተው ስብሰባ ላይ የባንኩ ሰራተኞች እኛን የቀጠረን ባንክ የግል ተቋም ነው። ስለዚህ ላንተ የምንሰጠው መልስ የለንም ብንናገርም የሚመጣ ለውጥ የለም በማለት ያለምንም ፍሬ ነገር ሳይግባቡ ከስብሰባው እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል።
    በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ምንም ዓይነት ወንጀልና ጥፋት ሳይኖረው ስርዓቱ በውስጡ ካለው ያለመተማመንና መጠራጠር ሁኔታ በመነሳት ንፁሃን ዜጎችን እያንገላታና በቂ ማስረጃ ሳያገኝ እያሰቃያቸው እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።