Monday, June 29, 2015

በባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኘው “ ያለም ብርሃን ሆስፒታል የተሰኘውን ህክምና የሚሰጠው ህዝባዊ አገልግሎት ደካማ በመሆኑ ምክንያት በግንቦት ወር ብቻ በርካታ እናቶች በወሊድ ምክንያት እንደሞቱ ተገለጸ።



በአማራ ክልል፤ ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኘው ያለም ብርሃን እየተባለ የሚጠራውን ሆስፒታል የሞያተኞችና የማተርያል አቅርቦቱ አነስተኛ በመሆኑ የተነሳ ለህዝቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ደካማ መሆኑና በዚህም ምክንያትም በግንቦት 2007 ዓ/ም ብቻ ከ 85 በላይ እናቶች ሲወልዱ መሞታቸውን ግንቦት 29/2007 ዓ/ም የወጣው ሪፖርት አስታውቀዋል።
   በወሊድ ምክንያት በሆስፒታሉ ውስጥ ከሞቱት እናቶች ውስጥ ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል ታፈሰች ይልማ፤ አደሬ ባህሩና አለሚቱ ታዘዘ የተባሉ የሚገኙባቸው ሲሆኑ የሞመታቸው ዋና ምክንያትም ምጥ ተይዘው ወደ ሆስፒታሉ በሚሄዱበት ግዜ ባፋጣኝ ተቀብሎ የሚያስተናግድ ባለሞያና የተሟላ የህክምና መሳርያ ባለመኖሩ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።