Monday, June 29, 2015

ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ዩንቨርስቲ በተካሄደው አስመሳይ ምርጫ ላይ ኢህአዴግ ስለ ተሸነፈ የተጀመረውን የድምፅ ቆጠራ እንዲቓረጥና ኮረጀውን በስርዓቱ ካድሬዎችና ወታደሮች እንዲሰረቅ መደረጉን ተገለፀ።



የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ  በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 18/ 2007 ዓ/ም ሌሊት ላይ የድምፅ ቆጠራ በተጀመረበት ግዜ ኢህአዴግ መሸነፉን ያረጋገጡት የስርዓቱ ካድሬዎች ሙሉ በሙሉ የድምጹን ቆጠራ ከመጠናቀቁ በፊት 6 ሰዓት ላይ ኮረጀውን በመከላከያ ሰራዊት ተሰርቆ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።
    የምርጫ ኮረጀውን የሰረቁት የምስራቅ እዝ፤ የ13 ክፍለጦር ወታደሮች እንደሆኑ የገለፀው መረጃው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ድምፃችን ሆን ተብሎ በስርዓቱ ተጭበርብረዋል በማለት ወደ ሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጥርያቸው ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙና ተቃውማቸው እየቀጠሉ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።