Sunday, July 5, 2015

የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች የመታወቂያ ካርድ ለማውጣት 200 ብር ለመክፈል እየተገደዱ መሆናቸውን ከከተማው ያተገኘው መረጃ አስታወቀ።



በትግራይ ምእራባዊ ዞን የሑመራ ከተማ ነዋሪ የመታወቂያ ካርድ ለማውጣት እስከ 200 ብር እንዲከፍል በስርዓቱ ካድሬዎችና አስተዳዳሪዎች እየተገደዱ መሆናቸው የገለጸው መረጃው፣ ህዝቡ ግን ይህንን ቅንነት የጎደለው አካሄድ በመቃወም፣ ብሶቱን እየገለፀ መሆኑን መረጃው አስታውቋል።
    በከተማው ውስጥ እንደዚህ አይነቱ ህገ ወጥ አሰራር ከረጅም ግዜ ጀምሮ እየተሰራበት ቢቆይም፣ በተለይ በቅርብ ቀን ጀምሮ ግን የስርዓቱ ካድሬዎች የመታወቂያ ካርድ  ለማውጣት ከመጠን በላይ እያስከፈሉ፣ ትርፉን ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።