Sunday, July 5, 2015

የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምክንያት፣ በስርዓቱ ላይ ያላቸው ጥላቻ እየገለፁ መሆናቸው ከከተማዋ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት፣ በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት ከገቢያቸው የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ እያስገደዳቸው በመሆኑ፣ መክፍል ተስኗቸው ድርጅታቸውን እየዘጉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው፣ ይህ በላያቸው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ፍትሃዊ ያልሆነውን የግብር አከፋፈል እንዲሻሻልላቸው ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረቡትን አቤቱታ አስካሁን መፍትሄ ሊያገኙበት እንዳልቻሉ ተገለፀ።
    ከአቅማቸው በላይ ግብር እየከፈሉ ከሚገኙት ወገኖች ውስጥ- አለነ አባይ 26 ሺ ብር፤ ሓሰን ስዒድ 55 ሺ 32 ብር፤ ማውጫ ገ/መድህን 13 ሺ 409 ብር፤ ቀሺ በየነ 90 ሺ 424 ብር፤ አብርሃ ገ/ፃዲቅ 19 ሺ 530 ብር፤ ንግስቲ ገብረፃዲቕ 15 ሺ 450 ብር፤ ግደይ ብርዧ 12 ሺ ብር፤ አቶ ካሕሳይ አለነ 15 ሺ 49 ብር ክፈሉ መባላቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
    በተለይ አቶ ጉዕሽ አብርሃ የተባሉት የሆቴል ባለቤት፣ የተወሰነባቸው ገንዘብ አልከፍልም በማለታቸው ምክንያት፣  በከተማው አስተዳዳሪዎች ድርጅታቸው ወደ ጨረታ ቢያቀርበውም፣ ህዝቡ ግን በዚሁ ጨረታ ውስጥ አንገባም በማለት መቃወሙን መረጃው አክሎ አስረድቷል።