Sunday, July 26, 2015

በሰሜን እዝ የሚገኙት የኢህአዴግ ስርዓት መከላከያ ሰራዊት አባላት ሳያምኑበት ቦንድ እንዲገዙ እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።



በሰሜን እዝ የሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን ቦንድ ግዙ በተባሉበት ሰዓት ሊቀበሉት ባለመቻላቸው ምክንያት በአሁኑ ግዜ በእዙ የበላይ ባለስልጣናት በተመራው ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
    ወታደሮቹ በስብሰባው ላይ ካነሱት የተቃውሞ ሃሳብ መካከል እያወጣነው ያለው ገንዘብ በምን ስራ ላይ እየዋለ ነው? እስካሁን የመጀመሪያ ቦንድ የከፈልንበት ደረሰኝ እንጂ የሁለተኛ የቦንድ ደረሰኝ አልመጣልንም ይህ ደረሰኝ ሳይመጣልን ለሶስተኛ ግዜ የቦንድ ክፍያ አንከፍልም በማለት ላቀረቡት ትክክለኛ ሓሳብ አጥጋቢ መልስ መስጠት የተሳናቸው የመድረኩ መሪዎች ይሳጣችኋል ዝም ብላችሁ የተባላቹሁትን ክፈሉ በማለት እያስገደዷቸው እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።