Sunday, July 26, 2015

የባህርዳር ከተማ ከንቲባ የህዝብና የሀገርን ሃብት ለግል ጥቅሙ አውሎታል ተብሎ ለግዜው ቢያዝም በአጭር ግዜ በመፈታቱ ምክንያት ህዝቡ እየተቃወመው እንደሚገኝ ተገለጸ።



    በአማራ ክልል፤ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ የሆነው ይልቃል አላምረው የተባለው የስርዓቱ ካድሬ ለመሰረተ ልማት እንዲውል ተብሎ ከተመደበው በጀት 165 ሺ ብር ለአንዳንድ ስራ ማከናወኛ ብሎ ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅሙ ስላዋለው ሓምሌ 5/ 2007 ዓ/ም ለተወሰነ ሰዓታት ተይዞ ሲያበቃ ያለ ምንም ማጣራት የክልሉ ባለስልጣናት ተሯሩጠው እንዲፈታ ማድረጋቸውን ተገለፀ።
   መረጃው በማከል የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ገንዘቡን ያጠፋፋው ባለስልጣን ህጉ በሚያዘው መሰረት በሚመለከተው ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበትና ጉዳዩን ተጣርቶ ገንዘቡን ማስረከብ ሲገባው በባለስልጣኖች ትእዛዝ በመፈታቱ ተቃውማቸው እያሰሙ መሆናቸውና በተለይ የባለስልጣኑን ብልሹ ተግባር የሚያውቁት ሸነሺ ይመርና ቴዲ ግርማ የተባሉ ሰዎች ወንጀለኛው የፈቱት ባለስጣናት ድረስ በመሄድ የተቃውሞ ሃሳባቸው ማቅረባቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።