Saturday, July 4, 2015

በሸራሮ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ከፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በብድር የወሰዱትን ገንዘብ አልወሰድንም በማለት ተመልሰው ገንዘቡን አጠፋፋኸው ብለው ለፋይናንስ ሰራተኛው ማሰራቸውን ተገለፀ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ሸራሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎችና አዛዦች ከከተማው ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሰራተኛውን እያስፈራሩና በእምነት ስጠን እያሉ የወሰዱትን ከ100 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ አልወሰድንም ብለው በመካድ የህግ አክባሪዎች መስለው በመቅረብ ገንዘቡን የሰጣቸው ንፁህ ዜጋ ላይ የሃሰት ክስ በመመስረት እስርቤት ውስጥ ማስገባታቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው አስታወቁ።
    ባሁኑ ጊዜ ታስሮ የሚገኘውን የፋይናንስ ሰራተኛው ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ እኔ ያጠፋሁት ገንዘብ የለም፤ አስተዳዳሪዎቹና አዛዦቹ ከተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን በእምነት አበድረን ብለው ወስደዋል ብሎ ለማስረዳት ቢሞክርም ዳኞቹ ግን ከባለስልጣኖቹ ጋር በመተባበር የሰጠኸው ቃል ተቀባይነት የለውም በማለታቸው ምክንያት እስር ቤት ሁኖ ፍርዱ እየተጠባበቀ መሆኑንና አምስት ዓመት የሚያህል  ሊያሳስረው እንደሚችል መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።