Saturday, July 4, 2015

በወልቃይት ወረዳ ተሰማርተው እየሰሩ የሚገኙት የፖሊስ ሰራዊት አባላት መሳርያቸውን ሽጠው ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ወልቃይት ወረዳ፤ ዓወርቂ በተባለው አካባቢ ተሰማርተው እየሰሩ ከሚገኙ አንዱ የሆነው መሃሪ የተባለ የኢህአዴግ ብዱን ፖሊስ አባል መሳርያውን ሽጦ ለግል ጥቅሙ እውሎታል ተብሎ መታሰሩን ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር በፖሊሶቹ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮችና ሚሊሻዎች ከአስተዳዳሪዎች ጋር በመተባበር መሳርያና ጥይቶችን በመሸጥ የማይገባቸው ሃብት እያካበቱ መሆናቸውንና በዚህም ምክንያት የማን እንደሆነ በማይታወቀው መሳርያ በኑፁኃን ህይወትና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩና ህዝቡ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ስራውን እንዳያሳልጥ ተቸግሮ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስታውቋል።