Saturday, July 4, 2015

በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ባለትዳር ሴቶች በመድፈር ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ።



   በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች በባለትዳር ሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት እየፈፀሙ እንዳሉ የገለፀው መረጃው ከነዚህ አፀያፊ ተግባር ላይ ከተሰማሩት መካከልም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ሓጎስ የተባለ ሲሆን እሱ ሰኔ 8 2007ዓ/ም ጥቃት ሲፈፅም እጅ ከፈንጅ ስለ ተያዘ ለጊዜው በተበዳዮች ተከሶ የታሰረ ቢሆንም የህዝቡ ስሜት ከተረጋጋ በኋላ ይፈቱታል የሚል ስጋት በህብረተሰቡ ዘንድ በሰፊው እየተነገረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
    የህወሓት/ኢህአዴግ አስተዳዳሪ የሆኑት ካድሬዎች ስልጣናቸውን ተጠቅመው በሴቶች ላይ እየፈጸሙት ያለው ፆታዊ ጥቃት በኢሮብ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በመላው ሃገራችን እየተካሄ የቆየ ያለ አስነዋሪ ተግባር መሆኑንና በዚሁ አስነዋሪ ድርጊት ቤተሶቦችና ባለትዳሮች እየተበተኑ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።