Saturday, July 4, 2015

በአብደ ራፊዕና አብርሃ ጅራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ዜጎቻችን የአካባቢው ተወላጆች ንብረታቸውን እየቀሙ እያባረሯዋቸው እንደሚገኙ ታወቀ።



   ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመልክተው በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በአውደ ራፊዕ አካባቢ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑት በእርሻ የሚተዳደሩ ኢንቨስተሮችና ሌሎች በክልሉ ተወላጆች ንብረታቸውንና መሬታቸውን እየተቀሙ ከቦታው እየተባረሩና በፀጥታ አካላት ወደ እስር ቤት እየተወሰዱና ደብዛቸው እየጠፉ መሆናቸው ተገለፀ።
    እንደዚህ አይነት ጥቃት እየደረሰባቸው ካሉት ሰዎች ለመጥቀስ ያህል መብራህቶም ወለተንሳይ የተባለ ኢንቨስተር ከመሬትህ ልቀቅ ስላሉትና አለቅም ህጋዊ መሬቴ ነው በማለቱ የተነሳ በእስር ወደ አብርሃ ጅራ መወሰዱ የገለፀው መረጃው ቤተሰቡ ደግሞ አብርሃ ጅራ ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ሁኔታውን በሚጠይቁበት ጊዜ በአስተዳዳሪዎችና በፖሊስ አዛዦች አናውቅም የሚል መልስ እንደሰጧዋቸው ለማወቅ ተችሏል።
   በተመሳሳይ በአካባቢው የኢህአዴግ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች የዘር ግጭትና የፖለቲካ ልዩነት የፈጠረው ብልሹ አሰራር ምክንያት በብሄር በሄረሰቦች መካከል ሰኔ 8/ 2007 ዓ/ም በአውደ ራፊዕና አብርሃ ጅራ አካባቢ በትግራይ ክልል ተወላጆች ላይ አላስፈላጊ እርምጃ እየተፈፀመ እንዳለ ባለፈው የዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወሳል።