Wednesday, July 1, 2015

በአዲ-ነብርኢድ አካባቢ ከመጠን በላይ ጭና ስትጓዝ የነበረች የማእከላዊ እዝ ፓትሮል መኪና ከህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨትዋ ምክንያት ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።



በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ አዲ ነብርኢድ፤ ልዩ ቦታው ማይ ዓሶ በተባለው አካባቢ ከሽሬ ተንስታ ወደ ሽራሮ ትጓዝ የነበረችው ታርጋ ቁጥርዋ መከ 01226 የሆነችው የማእከላይ እዝ ፓትሮል መኪና የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨትዋ ምክንያት በፓትሮልዋ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ ሁለት ሲሞቱ ሌሎች በከባድ መቁሰላቸውን ታወቀ።
     በአደጋው ወቅት ከሞቱት ውስጥ የመቶ አለቃ ደምሴና ወታደር ትካቦ ወልዱ ሲሆኑ በከባድ ከቆሰሉም የመኪናዋ ሹፌር የሆነው ወታደር አለልኝ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።