Thursday, December 20, 2012

በሞስሊሙ ማህበረሰብ መካነ መቃብር መፍረስ ምክንያት በዓዲ-ግራት ከተማ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ቷውቋል ።


ከዓዲግራት ወደ ዛላምበሳ በሚወስደው የመኪና መንገድ በተለምዶ ቀርሰበር እየተባለ በሚጠራው አከባቢ የሚገኝ የሞስሊም የመቃብር ቦታ ነባሩን የአስፋልት መንገድ ለማስፋት በሚል ምክንያት መንግስት መቃብሩን በዶዘር በመቆፈሩ በከባቢው የተቀሰቀሰው የሞስሊም ማህበረሰብ ተቃውሞ የክርስትና እምነት ተከታዮችና የብሄረ አፋር አባላት ድጋፍ ተጨምሮበት ተጠናክሮ ቀጥላል ።
የብሄረ አፋር ተወላጆች ወደ ምስራቅ ትግራይ ዞን መስተዳድር ቢሮ ድረስ በመሄድ የወገኖቻችንን አጥንት የተቀበረበትንና ለብዙ አመታት ተከብሮና ተጠብቆ የቆየ መካነ መቃብር ህዝቡን አስቀድማችሁ ሳታማክሩ በማን አለብኝነት መቆፈራችሁ ለህዝቡ ባህልና ልማድ ባአጠቃላይ ለሰብአዊ ክብር ያላችሁን ንቀት የሚያመለክት ነው በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል ።