Monday, December 10, 2012

በኢህአደግ ስርዓት አሰራር ያልተደሰቱ በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖሊስ አባላት ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑ ቷውቋል፣


-->


የኢህአደግ መንግስት ከግዜ ወደ ግዜ እየተጠናከረ የመጣውን የህዝብ ተቋውሞ ለመጨፍለቅ ሲል እየወሰደው ያለ የሃይል እርምጃ ያላስደሰታቸው በክልሉ የሚገኙ በርካታ የፖሊስ አባላት ስራቸውን ጥለው እየለቀቁ ነው፣
የክልሉ ባለስልጣናት ስራቸውን የሚለቁ የፖሊስ አባላት ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን ስላሳሰባቸው ከተመደቡበት የመንግስት ስራ በፍላጎታቸው የለቀቁ የፖሊስ አባላት ሁሉ ከጥቅምት 2005 ዓ/ም ጀምሮ በምድብ ስራቸው እንዲገኙ የሚል ጥብቅ መመሪያ ከክልል ወደ ሁሉም ዞኖች እንዲተላለፍ መደረጉን ቷውቋል፣
በአሁኑ ጊዜ በመላ ሃገሪቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው የእስራትና ግድያ ተግባር በመቋወም መደበኛ ስራቸውን ጥለው የሚለቁ የፖሊስ አባላት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የኢህአደግን ስርዓት እንደስርዓት ስጋት ውስጥ መሆኑን ያመለክታል፣