Tuesday, January 1, 2013

በአዊ ዞን በሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች ከ 12 ሚልዮን ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ መባከኑ ቷውቋል።

በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ በዳንግላ ከተማ ከታህሳስ 10-19,2005 ዓ/ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሃላፊ አቶ ገብያውና ወ/ሮ ይዛኑ በተሰጠ የኦዲት ስልጠና እንደታየው በያዝነው ዓመት 12 ሚልዮን ብር በዞኑ የመንግስት መ/ቤቶች መጠፋፋቱ በባለሞያዎች መረጋገጡ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት ገንዘቡ ሊባክን የቻለው በአከባቢው የሚገኙ ከፍተኛ የኢህአደግ መንግስት ባለስልጣናት ከፋይናንስ ባለሞያዎች ጋር በመመሳጠር አለአግባብ ወጪ እንዲሆን ተደርጎ የባከነ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።