Thursday, January 10, 2013

በሃረር ከተማ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሃይማኖት ነጻነት ይከበር በማለት ታህሳስ 27,2005 ዓ/ም የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።

በከተማዋ በአራተኛ መስጊድ ሲካሄድ የነበረውን የሞስሊሙ ህብረተሰብ ተቋውሞን በሃይል ለመጨፍለቅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መስጊዱ ጥሰው በመግባት በህገመንግስቱ የሰፈረውን ሃይማኖታዊ ነጻነቱንና መብቱን እንዲጠበቅለት በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቅ በነበረው ህዝብ ላይ ጥይት በመተኮስ አንዲት ዜጋ መግደላቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በመላ አገሪቱ የሚገኙ የሞስሊም ህብረተሰብ ሃይማኖታችን ይከበርልን ፤ በመረጥነው የሞጅሊስ አባላት እንመራ ፤ የሃይማኖት ነጻነት ይከበር ፤ መንግስት እጁን ያንሳ በማለትና አህባሽን በመቃወም ድምጻቸውን ማሰማት ከጀመሩ አንድ ዓመት ቢሞላቸውም እስካሁን ድረስ በመንግስት የተሰጣቸው አወንታዊ ምላሽ የለም።