Thursday, January 10, 2013

በመጭው ሚያዝያ የአከባቢና የማማያ ምርጫ አስፈጻሚ ለመምረጥ በመቐለ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው አሰራር የምርጫ ስነ-ምግባር ደምብን ያልተከተለ መሆኑን ቷውቋል።

በምርጫ ስነ-ምግባር ደምብ መሰረት ለምርጫ አስፈጻሚነት የሚመረጡ ዜጎች ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የተውጣጡና ከፖለቲካ ድርጅት አባልነት ነጻ መሆንን ይጠይቃል። በመቐለና በሁሉም በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች የተመረጡ የምርጫ አስፈጻሚዎች ግን ሁሉም የህወሓት አባላት በመሆናቸው ሂደቱ የምርጫ ስነ-ምግባር ደምብን አልተከተለም በማለት ቅሬታቸውን የሚገልጹ ወገኖች አሉ።
ህዝቡ የምርጫ ካርድ ከየፖሊስ ጣብያው እንዲወስድ እየተነገረው ሲሆን ፤ የፖሊስ አባላትም በየቤቱ እየዞረ ህዝቡን የምርጫ ካርድ እንዲወስድ እያስገደዱት ነው ፣ እስካሁን ድረስ የምርጫ ካርድ የወሰደው ህዝብ ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ ቷውቋል።
በመቐለ ከተማ በዓይደር ክፍለ ከተማ ሻለቃ ምሩጽ(ወዲ-ዓድዋ) የተባለ የፖሊስ ሃላፊ በራሱ ትእዛዝ ፖሊስ ከቀበሌ ጋር በመተባበር ህዝቡን ካርድ እንዲወስድ እያስገደደው ሲሆን ህዝቡም መረጥን አልመረጥን ያው ነው ፥ የሚመጣ ለውጥ የለም ፥ በሚል ለምርጫው ብዙም ትኩረት እንዳልሰጠው ለማወቅ ተችለዋል።
የክልሉ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆኖ በመስራት ላይ የሚገኝ አቶ ወንድሙ ጓላ የተባለ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ዘመድ ሲሆን ሁኔታው የስርዓቱ ቁንጮዎች እርስበራሳቸው በዝምድና የተሳሰሩ መሆናቸውን ያመለክታል።