በጸረ-ሽፍታ ስም ሲንቀሳቀስ የነበረው አስማረ ፤ የአከባቢው ኗሪዎችን ፤ የት ነበራችሁ ? ፤ ከተቃዋሚ
ሃይሎች ጋር ተገናኛችሁ ወዘተ በሚል ሰበብ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እለታዊ ህይወታቸውን በአግባቡ እንዳይመሩ መውጫና መግብያ በማሳጣት
በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግፍ በመፈጸም ኗሪዎችን ያማረረና የስርዓቱ ታማኝ የነበረ ሲሆን በእጁ ጨብጦ ይዞት በነበረ የእጅ ቦምብ የተነሳ
በስተት በስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት በተተኮሰበት ጥይት መስከርም 1,2006 ዓ/ም መገደሉን ታውቋል።
የኢሀዴግ ስርዓት አገልጋይ በመሆን የአከባቢውን ህዝብ ምክንያት እየፈጠረ ሲያሰቃይና ሲገድል የነበረው አስማረ
የሞት ዜና ከተሰማ ብሁዋላ የአከባቢው ህዝብ መደሰቱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።