የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ጋር በመሆኑ ፋሽሽቱን የደርግ ስርዓት ለመደምሰስ ባደረገው
መራራ ትግል ከፍተና አስተዋፆ ያደረጉ ነባር ታጋዮች በአሁኑ ጊዜ ከሰራዊቱ ተሰናብተው ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው የግል ህይወታቸውን
በመምራት ላይ ይገኛሉ ። የኢህአዴግ ስርዓት የጸጥታ ሃይሎች በያዝነው ሳምንት ታጋዮቹ ዋርዲያ በመውጣት አከባቢያቸውን እንዲጠብቁ
በኢህአዴግ መንግስት መመሪያ ቢሰጣቸውም እድሚያችን ገፍታል ፤ ተዳክመናል መንግስት በአሁኑ ጊዜ እኛን መርዳት እንጂ ተመልሶ እንድንጠብቀው
ሊጠይቀን ባልተገባው ነበር በማለት ተቃውማቸውን ገልጸዋል።
በታጋዮቹ
ተቃውሞ የተቆጡ የከተማዋ የመስተዳድር አካላትና የጸጥታ ሃላፊዎች የታዘዛችሁትን የማትፈጽሙ ከሆነ የታጠቃችሁትን ትጥቅ እንድታስረክቡ
ይደረጋል በማለት ታጋዮችን ለማስፈራራት ሞክረዋል። ነገር ግን ታጋዮቹ የታጠቅነው ትጥቅ በደማችን ያመጣነውና እራሳችንን ለመጠበቅ
መያዝ የሚገባን ነው ፥ ያስታጠቃችሁን ትጥቅ ያለ ይመስል አስረክቡ ልትሉ አይገባም ። በህይውት እስካለን ድረስ ትጥቃችን በፍጹም
አናስረክብን በማለታቸው በመሃከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ በውጥረት ላይ እንደሚገኙ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ይቻላል።