ሰራዊቱን የሚክዱ ወታደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱና ከክፍለ ጦር አመራር በታች ባሉ ወታደራዊ
አዛዦች ላይ እምነት እያጣ የመጣው የኢህአዴግ መንግስት በመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው የሚገኙ አሃድዎችን በማሰባጠር እንደ አንድ
አሃዱ በማዋቀር ለስርዓቱ ታማኝ በሚባሉ አዛዦች እንዲመሩ እያደረገ ነው።
የሰው ሃይላቸው በመመናመኑ ምክንያት በአንድ አሃዱ እንዲደራጁ ከተደረጉት ክፍለጦሮች መካከል በሰሜን እዝ
የ 14ኛ ና የ 19ኛ ክ/ጦሮች ይገኙበታል ። በነዚህ ክፍለ ጦሮች የነበሩ አዛዦች በግምገማ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገ ሲሆን
ክፍሎቹም ተጨፍልቀው በአዲስ አመራር እንዲመሩ ተደርጓል።
የሰባት ዓመታት አገልግሎታቸው ጨርሰው ከሰራዊቱ ለመሰናበት ያነሱትን ጥያቄ ስላልተመለሰላቸው ከክፍላቸው
በመጥፋት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ የሰራዊቱ አባላት ከያሉበት እየተለቀሙ ወደ ሰራዊቱ እንዲመጡ በማድረግ የተመናመነውን የሰው ሃይል
ለሞምላት እየተሞከረ ነው።