የኢህአዴግ ስርዓት በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ሳያወያይና ሳያሳምን አባልነትን ማእከል ያደረገ
አዲስ አሰራር በክልሉ በሚገኙ ሁሉም የመንግስት መስሪያቤቶች በክልሉ ባለስልጣናት በኩል ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ከነሃሴ
20,2005 ዓ/ም ጀምሮ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ያለዱጎማና የጡረታ አበል ከመደበኛ ስራቸው እየተነሱ እንዲባረሩ እየተደረገ
መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ከየመንግስት መ/ቤቱ እየተባረሩ ያሉ ሰራተኞች ብቃታቸው ተመዝኖ ሳይሆን አዲስ የተባለውን አሰራር እንደምክንያት
በመጠቀም በጥላቻ ዓይን የሚመለከቷቸው ሰራተኞችን እንደ አንድ ዋና የኢህአዴግ ስርዓት ተቋዋሚ በመቁጠር እንዲባረሩ የተደረጉ ናቸው።
ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል ሴቶች የሚገኙባቸው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ችግር ላይ ይገኛሉ።