Monday, May 5, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የሃገሪቱ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት ሚያዝያ 10 / 2006 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የእጅ ቦምብ መፈንዳቱ ታወቀ ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት ሚያዝያ 10 ንጋት  በ11፣00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በቦርዱ ፅህፈት ቤት የእጅ ቦምብ መፈንዳቱን የገለፀው መረጃው በዚህ የተደናገጡ ሽብር የገባቸው የኢ.ህ.አ.ደ.ግ ባለ-ስልጣናት ድግሞ ከአንድ አመት በኋላ የሚካሄደውን ሃገራዊ ምርጫ ለማሰናከል ተቃዋሚ ድርጅቶች ሆን ብለው የፍፀሙት ነው በማለት እየወነጀሏቸው እንዳሉ ታወቀ።
   በተጨማሪም በከባድ ስጋት የወደቁት የወያኔ ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ባለ ስልጣናት ለምርጫ ቦርዱ ፅህፈት ቤትና አከባቢዉን በፌደራል ፖሊሶች በፁኑ እንዲጠበቅ መምሪያ እንዳወረዱ የደረሰን መረጃ አመለከተ።