Monday, May 5, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ በመሬት ሸንሻኝ የስርዓቱ ካድሬዎችና በህዝብ መካከል በተፈጠረው አለመረዳዳት ምክንያት በርከት ያለ ህዝብ እንደታሰረ ምንጮቻችን ገለፁ።



በቃፍታ ሑመራ ወረዳ ሰፊ መሬት እያለ ግን ደግሞ ስርዓቱ በሚያደርገው የማዳላት ስራ ምክንያት ችግር መፈጠሩን የገለፀው መረጃው በውጤቱም አስተዳዳሪዎች ያወረዱትን መምሪያ በመቃወም መሬት ወደ ሚያድሉበት ቦታ አንሄድም በማለታቸው የተነሳ በካድሬዎች ተዘጋጅቶ የነበረው የመሬት ክፍፍል ፕሮግራም ተሰናክሎ እንደቀረ ለማወቅ ተችሏል።
     የስርአቱ መሬት ሸንሻኝ ካድሬዎች መሬት ወደ ሚታደልበት ቦታ ለብቻቸው በመሄድ በቦታው ደርሰው ያለምንም ፍሬ እንደተመለሱ የገለፀው መርጃው በህዝቡ ተቃውሞ የሰጉ የስርአቱ ባለስልጣናት ነዋሪዎቹ በመሬት ክፍፍል አስታከው ሰበብ በመፍጠር ተቃውሞ ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል በማለት ለጠረጠሯቸው ከ150 በላይ የሚሆኑ ንፁሃን ወገኖቻችን በሚያዝያ 15 / 2006 ዓ/ም ከመኖሪያ ቤታቸውና ከስራ ገበታቸው በመሰብሰብ ወስደው እንዳሰሯቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።