Thursday, May 8, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የፖሊስ አባላት የታጠቁትን መሳርያ ተጠቅመው በከተማው ነዋሪዎች ላይ በደል እያደረሱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በሽሬ ከተማ የሚገኙ የፖሊስ ደህንነት አባላት የታጠቁትን መሳርያ ተጠቅመው በንፁሃን ወገኖች ላይ በደል እያደረሱ መሆናቸውና ከነዚህም የፖሊስ አባላት መካከል አስራ-አለቃ ተስፋይ የተባለው ቀደም ሲል በሽሬ እንስስላሴ ወረዳ በፍርድ ቤት ውስጥ ተመድቦ እየሰራ የቆየ የከተማዋ ፖሊስ አባል ተኩስ ከፍቶ እደጋ ማድረሱ ተገልጿል።
    አስራ-አለቃ ተፋይ በታጠቀው መሳርያ ተጠቅሞ ቀበሌ 03 መንደር 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተኩሶ 2 ሰዎችን ማቁሰሉንና የ3 ልጆች እናት ለሆነችው ሚስቱም ከጥዋቱ 1፣00 ሰአት ላይ ሁለት ጥይት ተኩሶ እንደገደላት የገለፀው መረጃው በተፈፀመው ድርጊት ቅሬታ የተሰማቸው የሽሬ ከተማ ነዋሪዎችም በስርአቱና እሰቃቂ ግድያ በፈመው ግለሰብ ላይ ብሶታቸውን እንደገለፁ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።