Thursday, May 8, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን አስገደ ፅንብላ ወረዳ እንዳባጉና ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲክፍሉ በመጠየቃቸው ምክንያት በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አመራሮች ላይ ከባድ ተቃውሞ ማስነሳታቸው ተገለፀ።



የእንዳባ-ጉና ከተማ ነጋዴዎች የህወሃት ባለስልጣኖች በጠሩት ስብሰባ ላይ በሚሊዮን የሚገመት ግብር  እንዲከፍሉ በመጠየቃቸው ነጋዴዎቹ የተጠየቁትን የግብር ክፍያ ፍትሃዊ አይደለም ብለው እንደተቃወሙና አንከፍልም ካሉት ውስጥ አቶ ጌታቸው ወልቅየ፤ አቶ ፍፁም ታደሰ፤ አቶ ታደሰ ውቃልኝና ሊሎች የነጋዴዎች ማህበረሰብ እንባ እየተናነቃቸው ስሜታቸውን እንደገለፁ የደረሰን መረጃ አስታውቀዋል።
    መረጃው በማስከተል ስብሰባውን በመምራት ላይ የነበረው የከተማው ከንቲባ ብርሃነ ወረስ የተባለ የስርአቱ ካድሬ ነጋዴዎቹ የተባሉትን ግብር እንዲከፍሉ ቢያስፈራራቸውም በሁኔታው የተማረሩ ነጋዴዎች መፍትሄ ለማግኘት ብለው ወደ ትግራይ ምክትል አስተዳዳሪ በየኔ መኩሩ በመሄድ የተወሰነላቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ መሆኑና በዚህ ምክንያትም ለድህነትና ስደት መጋለጣችን አይቀሬ ነው ብለው ላቀረቡት አቤቱታ ምንም አይነት ውጤት እናዳላገኙለት መረጃው አክሎ አስረድቷል።