Saturday, July 5, 2014

በሱዳንና በሳውዲ አረብያ ሲኖሩ ቆይተው ወደ አገራቸው የተመለሱትና ባሁኑ ግዜ አበደራፍእ ከተማ ላይ በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩትን ኢንቨስተሮች ግብር ስለበዛባቸው እርሻቸው ትተው እንዲሄዱ እየተገደዱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣፣



በመረጃው መሰረት በአብ ደራፍዕ ከተማና አካባቢው በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ባለ ሃብቶች በኢህአዴግ ስርአት ካድሬዎች ማዳበርያ እንድትወስዱ መሬታችሁን ለኩት የሚል መመርያ በመስጠት የመዳበርያና የመሬት ግብር ባንድ ግዜ ከልክ በላይ የሆነ ክፍያ እንዲከፍሉ ስላስገደድዋቸው እናንተ ቆይታችሁም በአምላክ ሃይል ለሚመጣው ዝናብም ታስከፍሉናላቹህ መሬታችሁን ትተንላቹሃል በማለት ተቃውማቸው እንዳሰሙ ከቦታው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
     ተቃውሞው ካሰሙ ኢንቨስተሮች የተወሰኑትን ለመጥቀስ- አለባቸው መኳንንትና ዳኛቸው ከበደ( ከሱዳን የመጡ)፤ ስኢድ ሃሰንና ናስር ሙስጠፋ (ካሳውዲ አረብያ የመጡ) መሆናቸውና እነዚህ ከስደት ተመልሰው ራሳችንን ጠቅመን አገራችንን እንጠቅማለን ብለው በስራው የተሰማሩ ዜጎች እስካሁን በሰው ሃገር ተሰደን የሰበሰብነውን ገንዘብ ተጠቅመን ስራችን ስናከናውን ቆይተናል አሁን ግን አቅጣጫውን በሳተ ክፍያ ለኪሳራ ተጋልጠናል  በዚሁ ቅጥ ያጣ አካሄድም አገራችን ሊያልፍላት አይችልም በማለት ይዘውት የቆዩትን የእርሻ ቦታ ትተውት እየሄዱ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣