እነኝህ ከኢህአደግ ስረአት መከላከያ ስራዊት ሲያገለግሉ ቆይተው የተሰናበቱ ወተሃደሮች የአገልግሎት ግዝያቸው
ያበቃና እንዲሁም በኤች ኣይቪ ኤድስ በሽታ ተይዘው አታስፍልጉኑም ተብለው በስርአቱ የተባረሩት የሰራዊቱ አባላት “ራሳቸው እምቢ
ብለው ወጡ” የሚል የስንብት ወረቀት ስለተፃፈባቸው በሃገራቸው ሰርተው እንዳይኖሩ እንቅፋት ስለሆነባቸው በሽግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ
ምንጮቻችን ከተለያዩ ያገራችን አከባቢዎች አስረድተዋል፣፣
ይህ ተሰናባቾችን መሰረት አድርጎ የጠቀሰው
መረጃው “ መንግስት ራሱ አስናብቶን ሲያበቃ በእምቢተኝነት እንደወጣን
አስመስሎ የስንብት ወረቀት መፃፉ በሃገራችን ውስጥ ስርተን ኑሯችን እንዳንመራ እንቅፋት የሚፈጥር ሃላፊነታዊ የጎደለው አስራር ነው”
በማለት በሃላፊዎቻቸው የተሰጣቸው የስንብት ወረቀት በመቃወምና በመክሰስ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፣፣
ከስርአቱ መከላከያ ሰራዊት ሳንወጣ
በአዲስ አበባ መከላከያ ሰራዊት ፅህፈት ቤት በሰኔ 17/ 2006 ዓ/ም የእዞችና የክፍለጦር አዛዦች የተገኙበት ስብሰባ ላይ የስራዊቱ ባለስልጣናትና አባላቱ በማህበራዊ አገልግሎት እጥረት እየተቸገሩና
እየተራቡ በመሆናቸው በጀት ይጨመርላቸው በሚል ሃሳብ ባነሱበት ግዜ በአንድ በኩል 50 ብር ይጨመርላቸው ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ
100 ብር ይጨመርላቸው በሚል ነጥብ ላይ ከተከራከሩ በኋላ መጨረሻ ላይ100 ብር ብለው መወሰናቸውና በዋናው የመሰብሰብያ አጀንዳቸው
ግን ሳይስማሙ ተኮራርፈው እንደተበተኑ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል፣፣