Sunday, September 28, 2014

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የ24ኛ ክፍለ-ሰራዊት አባላት ወደ ከተማ በመግባት በሚፈጥሩት ግጭት የንፁሃንን ዜጎች ህይወት እየቀጠፉ በመሆናቸው የተነሳ የከተማዋ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ተገለፀ።



በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ የከተማዋን ፀጥታ እንዲጠብቁ ተብለው የተሰማሩ የ24 ክፍለ ሰራዊት አባላት የሆኑ ወታደራዊ ፖሊሶች(ወፖ) መስከረም 1/ 2007 ዓ.ም ከሆቴል ውስጥ ካገኙት ወታደር ጋር ተጋጭተው በተኮሱት የእጅ ቦንብ እራሳቸውንና ሁለት ሌላ ንፁሃን ዜጎችን ጨምረው ስለሞቱ የከተማዋ ነዋሪዎችና የተለያዩ ተቋማት ባለቤቶች በገዥው የኢህአዴግ ወታደሮች ላይ ያላቸው ጥላቻ ወደከፋ ደረጃ እያመራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው አክሎ- አምሳ አለቃ ሰለሞን የተባለ ወታደራዊ ፖሊስ። ሆቴል ውስጥ እየጠጣ ላገኘው ገበየሁ ለተባለ ወታደር ከነ ትጥቅህ ሆቴል ገብተህ መጠጣት አይፈቀድም ውጣ  ሲል ላወረደለት ትዕዛዝ በመቃወሙ ምክንያት ሊመታው በሚንደራደርበት ጊዜ ወታደር ገበየሁ ደግሞ በተኮሰው የእጅ ቦንብ እራሱንና ሊመታው የመጣውን ወታደር እንዲሁም በሆቴሉ ውስጥ ለነበሩ ሁለት ስቪሎች ጨምሮ በአጠቃላይ ያራት ሰዎችን ህይወት እንዳጠፋ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
   የኢህአዴግ ገዥው ስርአት ወታደሮች ሃላፊዎቻቸው እየተከተሉት ባለው የከፋፍለህ ግዛ አካሄዳቸው በውስጣቸው ምንም አይነት ጓዳዊ ፍቅርም ሆነ መተዛዘንና መረዳዳት ስለሌላቸው ክብራቸውን ለማስጠበቅና በጥቅማ-ጥቅም ምክንያት ሁሌ እንደሚገዳደሉ የደረሰን መረጃው አክሎ አስረድቷል።