Tuesday, September 30, 2014

በምእራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ፤ ብሎ ቀበሌ የሚገኙት አርሶ አደሮች በኦህዴድ ኢህአዴግ ገዢው መንግስት እየተገደሉ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



    ብምንጮቻችን መረጃ መሰረት በኦሮምያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞን፤ አምቦ ወረዳ፤ ብሎ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከረጅም አመታት ጀምረው ሲያርሱት የቆዩት ጉሮምቲ በመባል የሚታወቀው የእርሻ ቦታ ያካባቢው አስተዳዳሪዎች ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጡ አታርሱትም ብለው ስለ ከለከልዋቸው በተፈጠረው ግጭት ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ማጋጠሙን የደረሰን መረጃ ገለፀ።
     አርሶ-አደሮቹ ወደሚገኙበት ቦታ የተላኩት የመንግስት ሚልሻ ሃይሎች ሁኔታውን በሃይል ለመፍታት በሞኮሩበት ሰዓት በተፈጠረው ግጭት ላይ ተከተል ዶበጭ በተባለው ሚልሻ በተተኮሰ ጥይት ጎሳየ የተባለው አርሶ አደር ሲገደል ሌሎች ታጣቂዎች በተኮሱት ደግሞ 4 ንፁሃን ሰዎች ቆስሎው ወደ ወረዳው ሆስፒታል መወሰዳቸውን መረጃው የገለፀ ሲሆን፣ በተፈጠረው ግጭት የተቆጡት ያካባቢው ነዋሪዎችም ወደ ወረዳው አስተዳደር በመሄድ ብሶታቸውን ቢያቀርቡም አስተዳደሩ ግን አስፈራርቶ እንደመለሳቸው ምንጮቻችን ከቦታው በላኩልን መረጃ ሊታወቅ ተችሏል።