የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል
ላመታት በጭቁኖች ወገኖች ላይ ተጭኖ የነበረውን የኃላ ቀርነትና ፀረ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የማስወገድ ትግል ቢሆንም ይስልጣን ጥማቸው
እንጂ የህዝቡን ፍላጎት የሟሟላት ልቦና ባልነበራቸውና የክህደት አስተሳሰብ በተጠናወታቸው መሪዎች የተነሳ የህዝዝቦቹ መስዋእትነት
ዋጋ ቢስ ሆኖ እንዲቀር አድርገውታል።
ህዝቦች ህግ ፊት ያለምንም አድልዎ እንዲዳኙ፤ የበላይነት አስተሳሰብ
ተወግዶና የዜጎች ሰብአዊ ክብር ተጠብቆ ባገራቸው ላይ ያለ ምንም ልዩነት የሃብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ፤ ሃሳባቸውን በነፃ የመግለፅና
የመቃወም መብታቸው እንዲከበርላቸው የሁሉም ህብረተስብ ፍላጎት ቢሆንም የእድል ጉዳይ ይመስል ህዝቡ የዚሁ ቀና አካሄድና አስተሳሰብ ተጠቃሚ ሊሆን አልቻለም።
የመልካም አስተዳደር ጉዳይ የሰላም፤ የመረጋጋት፤ በእድገት የመጠቀ ህብረተሰብ
የመፍጠርና በአጠቃላይ የሃገሪቱን እድገት በማፋጠን በኩል ትልቅ ሚና
የሚጫወት መሆኑ ቢታወቅም በዚሁ ቀና አስተሳሰብ መራመድ ተጠቃሚዎች ያልሆኑ ስርአቶች ግን ነጋ ጠባ ለማስመሰል ብቻ ሲሉ እንደ ዋነኛ
አርእስት አድረገው በማቅረብ ለማደናገርያ እንደሚጠቀሙበት የወያኔ ኢህአዴግን ስርአት ተግባር በማየት ሁኔታውን በግልፅ መረዳት ይቻላል።
የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች ወደ ስልጣን ከወጡበት ማግስት ጀምረው ስለ
መልካም አስተዳደርንና ሌሎች አርእስቶች እያነሱ በተለያዩ መድረኮችና የሚድያ ማሰራጫዎች እንደ ትልቅ አጀንዳ በመውሰድ ይናገሩባቸዋል
ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የህዝብ መድረኮች በማዘጋጀት በድለን ነበር፤ካሁን በኃላ አይደግመንም፤ ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን ወ.ዘ.ተ
የሚሉ የሚያስጎመጁ ሓረጎችን በመጠቀም የአዞ እንባ የሚያነቡ በተንኮል የተጠመቁና የተካኑ ፍጡራን መሆናቸውን ማንም ኢትዮጵያዊ ይውቃቸዋል፣
ይህ ፀረ ህዝብ አካሄዳቸውም በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች በስፋት እየተጠቀሙበት ያሉ መሰሪ ተግባራቸው መሆኑን ግልፅ ነው።
ባለፉት ሳምንታት በትግራይ ምእራባዊ አካባቢ በሁመራ ከተማ ውስጥ። መልካም
አሰተዳደርን አስመልክተው የአካባቢውን ህዝብ ሰብስበው ባወያዩበት ሰዓት የስብሰባው ተሳታፊዎች የሆኑትን የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች
ያለ አንዳች ፍርሃትና መሸማቀቅ የስርአቱን ብልሹ አስተዳደራዊ ሁኔታ
በተለይ ደግሞ በከተማው ውስጥ የሚገኙ የስርአቱ ሹማምንቶችንና እየፈፀሙት ያሉትን ፀረ ህዝብ አስራራቸውን ስሜት በተሞላበት መንገድ
ሂስ ሲያደርጉት ተስተውለዋል።
በስብሰባው ወቅት የተነሱት ጥያቄዎችና አስየየቶች በርከት ያሉ ቢሆኑም
ጥቂት እንኳር አንኳር የሆኑትን ለመጥቀስ-
- ባለቢላዎች ቤታቸውን አከራይተው ለራሳቸው ርካሽ በሆነ የመንግስት ወይም የቀበሌ ቤት እየኖሩ ድሃው ወገን
ግን መጠለያ እጥቶ በስቃይና በችግር እንዲኖር በመገደዱ ምክንያት መፍትሄ ይሆነኛል ብሎ ለሰራት ደሳሳ ጎጆም ከህግ ውጭ ነው የሰራሀው
እየተባለ በመንግስት ትእዛዝ እንደሚፈርስ፤
- የግብር አከፋፈል በሚመለከትም ስራው ከሚመለከታቸው አካላት ቅርበት ወይም ዝምድና ያለው ከሆነ የሚከፍለው
ግብር አንሰተኛ እንደሆነ ትውውቅ ከሌለህ ግን ከመጠን በላይ ለመክፈል እንደምትገደድ በዚህ መሰረትም ፍትሃዊ የግብር አከፋፈል እንደሌለ፤
- በመንግስት ድጎማ ተደርጎላቸው የመጡትን እንደ ሱኳር፤ ዘይትና ሌሎች ህብረተሰቡ የሚጠቀምባቸው አላቂ እቃዎች
በድብቅ ወደ ሌላ ቦታ የተጓጓዙ እንደሚሸጡና ለህዝቡ እንዲያከፋፍሉ ተብለው ሃላፊነት የተሰጣቸው የከተማው ነጋዴዎችም ደብቀው በመሸጥ
ለራሳቸውና ተባባሪዎቻቸው ለሆኑት አስተዳዳሪዎች ጥቅም እያዋሉት መሆኑን፤
- ግብር በዝቶብኛል ብሎ ንግድ ፈቃዱን ያስርከበ ነጋዴ የሚሰራበት ድርጅት ሳይዘጋ ስራውን እየቀጠለ መሆኑ
እየታወቀ ችላ ማለት ይህም ህጋዊ ያልሆነ ነጋዴ እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆነ እንደሆነ የሚሉና ሌሎች በከተማው ባለስልጣኖች እየተፈፀሙ
የሚገኙ አስነዋሪ ተግባሮች በስፋት ተነስተዋል።
እነዚህ በከተማው ህዝብ የተነሱት ጥያቄዎችና እስተያየቶች የስርአቱ
መሪዎች ከላይ እንደተገለፀው ችግሮች ነበሩን፤ እናስተካክለዋለን በማለት እንደተለመደው ለህዝቡ ብለው የማያደርጉት ነገር እንደሌለ
በመጥቀስ የሚያድናግሩ ቃላቶችን ሲጠቀሙ ተሰምተዋል።
የተከበርህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ የወያኔ ስርአትና ተባባሪዎቹ አሁንም
ቢሆን የስልጣን እድሜአቸውን ለማስቀጠል ሲሉ በህዝቡ ደምና መስዋእትነት እየተረማመዱ በየቀኑ በሚፈጥሩት አስመሳይና የማይተገበር ቃላት ህዝባችንን እያታለሉና
ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን እየቀጠሉበት ነውና በሚካሄዱ አስመሳይ የስባሰባ አጀንዳዎችና ባዶ ተስፋዎች ሳትዘናጋ የልማትህ እደናቃፊዋች
የሆኑትን የስርአቱ ተላላኪዎች ልታውቃቸውና በመሰብሰብያ አዳራሻቸው ሆነህ ያሰማሀውን ተቃውሞ ይበልጡን ለማጠናከር ትግልህን አጣናክረህ
ልትቀጥልበት ይገባል።