Saturday, December 27, 2014

የአህፈሮም ወረዳ ነዋሪዎች ፍትህና መልካም አስተዳደርን አስመልክተው አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አባላት የቀረበላቸውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉት ተገለፀ።



ታህሳስ 3/ 2007 ዓ/ም በትግራይ ማእከላዊ ዞን ለሚገኙ የአህፈሮም ወረዳ ነዋሪዎች በክልሉ የፍትህ አባላት መልካም አስተዳደርና ፍትህን አስመልክቶ ሰብሰባ መካሄዱን የገለፀው መረጃው 3000 ያህል በስብሰባው ላይ የተሳተፈው ነዋሪ ህዝብ ይህን ጉዳይ በማስመልከት አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ምንጮቻን ከአካባቢው ያደረሱልን መረጃ አመለከተ።
    በህዝቡ እምቢተኝነት ስጋት ላይ የወደቁ የመድረኩ መሪዎች የስብሰባውን አካሄድ በመቀየር የባንዴራ ቀለም ያለበት ሦስት ሳጥን በማዘጋጀት አረንጋዴ ቀለም በተቀባው ፍትህና መልካም አስተዳደር በጥሩ ሁኔት እንደሚገኝ፤ ቢጫው ላይ የተወሰነ ፍትሕ ቢኖርም ጉድለቶች ይታያሉ፤ ቀይ ቀለም በተቀባው ሳጥን ደግሞ ፍትህ ይሁን መልካም አስተዳደር ፈፅሞ የለም የሚል የድብቅ ድምፅ መስጫ ተጠቅሞው አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ላቀረቡላቸው አማራጭ ሳይቀበሉና ሳጥኖቹን ሳይጠቀምባቸው መቅረታቸው በመልካም አስተዳደርና ፍትህ ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን የሚያመላክት እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።