በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በደቡብ ክልል፤ ኦሞ ዞን፤ ሃመር ወረዳ፤ ዲመካ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችን ግንቦት
16/2007 ዓ/ም በተካሄደው አስመሳይ ምርጫ ላይ እንዳይመርጡ መከልከላቸው የገለፀው መረጃው የደኢህዴን/ ኢህአዴግ ስርዓት ግን
በአካባቢው ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለህ በማለቱ ተቆጥተው ባካሄዱት ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፍ በኢህአዴግ ቡዱን ወታደሮች ከሚደርሳቸው
ጥቃት ለመከላከል በተፈጠረው ግጭን ሳብያ 100 የሚያህሉ ንፁሃን ዜጎቻችን ህይወታቸውን እንዳጡ ታውቋል።
በስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ከተገደሉት የተወሰኑትን
ለመግለፅ ያህል አቶ ጌታቸው ለማ፤ አቶ ጣሰው ቢያርግልኝ፤ አቶ ቢራራ ምንዳ፤ ወ/ሮ ሌሊቱ ቱፋ፤ አቶ ዳኘው ሸምሱ፤ አቶ ቃሲም፤
አቶ ኮት፤ አቶ ሳሊሕ ኢብራሂምና ሌሎችም እንደሆኑ መረጃው አስታውቋል።
ተቃውሞ እያካሄዱ ከነበሩ የዲመካ ነዋሪዎችና ተቃውሞውን
ለመበተን እየተንቀሳቀሱ ከነበሩ ወታደሮች ጋር በተፈጠረው ግጭት ሳብያ 5 የስርዓቱ ወታደሮች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውና
ለግዜው ስማቸው ያልታወቁ 100 የሚያህሉ ዜጎች ተገድለው አስከሬናቸው ጎዳና ላይ መጣሉን ባለፈው የዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል።