ምንጮቻችን እንደገለፁት በተለያዩ የመቀሌ ዩንቨርስቲ ጨንፈሮች ተቀጥረው ከሚሰሩ ሰራተኞች በየወሩ ደመወዛቸው የሚታገዱ ቁጥራቸው
ቀላል ያለ መሆኑን ከገለፀ በኃላ፣ በተለይ በዩንቨርስቲው የቴክኒክ ተባባሪዎች የሆኑ ሰራተኞች በትምህርት እና ስራ እድገት እንዲሁም
በመንግስት አሰራር የሚታይ ግልፅ ያልሆነ አሰራር እና ሌሎች መጥፎ አሰራሮች አስመልክተው የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው የህዳር ወር
ደመወዛቸው መታገዱ ለግዳዮች መሰረት ያደረገ መረጃ አመለከተ።
በመቀሌ ዩንቨርስቲ አስተዳደር የሰራተኞች መብት መጣስ በቀጣይነት እንደሚፈፀምና
ለዚህ በላያቸው ላይ የሚፈፀም ኢ-ዴሞክራስያዊ አሰራር ለሚቃወሙ ሰራተኞች ከደመወዛቸው መከልከል አልፎ ከስራ መባረር እና ማገድ
እርምጃ በመውሰድ ለሰራተኞቹ አንገታቸው እንዲደፉ እንደሚያድርጋቸው የገለፀው መረጃው፣ እንደዚህ አይነት አሰራር በሁሉም የአገሪቱ
ዩንቨርስቲዎች እና በተለያዩ የመንግስት ፅፈት ቤቶች እየተሰራበት የሚገኝ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑ መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።