በደረሰን መረጃ መሰረት ጀነራል ሞላ ሃይለማሪያም
በስልጣን ዘመኑ ለጉጅሌው የወያኔ ስርአት ለረጅም ግዜ በአየር ሃይል አዛዥነት ሲያገለግል ከቆየ በኃላ ባለፈው ግዜ በተለያዩ ምክንያቶች
ከነበረበት የስራ ሃላፊነት ወርዶ ታስሮ እንደነበረ የገለጸው መረጃው በአሁኑ ግዜ ደግሞ የብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከል ሃላፊ
ሆኖ እንደተመደበ ታወቀ።
መረጃው ጨምሮ
እንዳስረዳው ጀኔራል ሞላ አሁን ተመድቦበት ያለው ሃላፊነት በስራ ባልደረቦቹ በነበሩት ሰዎች አግባብ ያለው አመዳደብ አይደለም ከዚህም
በላይ ሊመራና ሊያስተዳድር አቅም ያለው እንደሆነ በመግለጽ አሁን ያለቦታው የተመደበበት ምክንያትም እራሳቸው ከፈጠሩት ስጋት ጋር በማያያዝ ሊቀየር ችሏል በማለት እየተነጋገሩበት
እንደሚገኙ ለማውቅ ተችሏል።