እንደምንጮቻችን ገለፃ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች
በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው የሚሰሩ አካላት በተጣለባቸው ሚዛኑን
ያልጠበቀ ከፍተኛ ግብር ምክንያት የስራ ፈቃዳቸውን እየመለሱ ስራቸውን ማቆማቸውን የጠቆሙት ምንጮቻችን መላክ በተባለ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ሆቴል ከአቅም በላይ 80 ሺህ ብር ግብር መጣሉን
ተከትሎ ግለሰቡ የስራ ፈቃዱ እንዲሰረዝለት መጠየቁን ገልፀዋል።
በመጨረሻም የደንበጫ ከተማ አስተዳደር
የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታደሰ ስለጉዳዩ በተደጋጋሚ ተጠይቆ ምንም ምላሽ ሊሰጥ እንዳልቻለ ታውቋል።