Tuesday, February 16, 2016

በሃዋሳ ከተማ በጥር 26 2008 ዓ/ም ሌሊት የተቃውሞ ፓምፒሌቶች ተበትነው እንዳደሩና በተለይ ደግሞ በመንግሰት ደርጅቶች በፖሊስ ጣቢያ፤ በወተሃደራዊ ካምፖች እንደተለጠፉ ተገለፀ።



   የተበተኑት የተቃውሞ ፓምፒሌቶች ከያዛቸው የተለያዩ መፈክሮች ለመጥቀስ፣ ብልሹ መንግሰት መልካም አስተዳደርን ሊያነግስ አይችልም፤ ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፍ ይቁም፤ በግፍ የተገደሉትን ንፁሃን ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው ካሳ ይከፈል፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወንጀለኛው የኢህአዴግ መንግሰት አይደራደርም፤ የኦሮም ህዝብ ትግል የሁሉም ክልሎች ትግል አጋር በመሆኑ በሰላማዊ ሰልፍ ንደግፍዎና ህዝባዊ መንግሰት ይቋቋም የሚሉ መልእክቶችን የያዘ መሆኑን መረጃው አስረድቷል።
    መንቀሳቀሻ ያጡ ወገኖች በአካባቢው የሚያደርጉትን የተቃውሞ  ወረቀት መበተን ገዥው ሰርአት ሚዲያዎችን ዘግቶና ተቆጣጥሮ የህዝብ ደምፅ በማፈን ይህንን መልእክት ያዘሉ ፓምፒሌቶችን  እየበተኑ ደምፁ እንዲሰማ ማደረጋቸው የሚደግፍ እንደሆነና፣ አንዳንድ የፖለቲካ ሙሁራኖችም ድጋፋቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸው መረጃው ጨምሮ አሰረድቷል።

No comments:

Post a Comment