ከስፍራው
የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው፣ በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን
ሁመራ ከተማ ሲካሄድ በሰነበተው ግምገማ ላይ በርከት ያሉ የስርአቱ የፍትህ አካላት በህዝብ ሰፊ ሂስ ሰለ ቀረበባቸው፣ እየታሰሩና እየተባረሩ መኖራቸውንና በዚህ መሰረት ደግሞ የሁመራ ከተማ አቃቤ ህግ የነበረ ሙሉጌታ ተክለና የምእራብ ዞን አቃቤ ህግ ቴዎድሮስ በሙስና ከስራቸው
እንዲባረሩ የተባሉ ሲሆኑ።
በተመሳስይ በቃፍታ ሁመራ ወረዳ አቃቤ ህግ የነበሩ ሄኖክ ሃይለና ኪዳነ ተስፋይ
እንዲሁም በሁመራ ከተማ ዳኛ የነበረ ሰለሙን የተባለ ሰው ፈጸመወት የተባለ ጉዳይ በመጣራት ሂደት ሲሆን፣ የቀረበላቸው ክስ እስከሚጣራ
በሚል በእሱር ቤት ውስጥ የሚገኙ እንኳ ቢሆኑም፣ ህዝብ ግን የገዥው ስርአት ባለ ስልጣናት ለተነሳው ህዝባዊ ስሜት ለግዜው ለማብረድ
በሚል እያባረሩና እያሰሩ ቢገኙም፣ ሙስና በማጥፋት ፍትህ ለማንገስ በዘላቂነት ይሰራሉ የሚል እምነት ህዝቡ እንደሌለው ምንጮቻችን
ከቦታው የላኩልን መረጃ አስታወቀ።
No comments:
Post a Comment