Sunday, June 11, 2017

በሐውዜን ወረዳ እና ውቅሮ ከተማ የሚገኙ መምህራን ደሞዛችን በትክክል እየተከፈለን አይደለም ሲሉ ገልፀዋል።



ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው፣ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ሓውዜን ወረዳ እና ውቅሮ ከተማ የሚገኙ መምህራን በሞያችን ሁለተኛ ዲግሪ እያለን በአንደኛ ዲግሪ እየተከፈለን ነው ያለ ሲሉ፣ ተናግረዋል።
በመሰረቱ የሃገራችን ስርዓተ ትምህርት ሕግ፣ አንደኛ ዲግሪ ያለው መምህር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲያስተምር ፤ሁለተኛ ዲግሪ ያለው ደግሞ በመሰናዶ ት/ቤት እንድያስተምር ተገቢ ሆኖ እያለ፣ እኛ ግን ሁለተኛ ዲግሪ ይዘን በሁለተኛ ደረጃ አብያተ ትምህርት እያስተማርን፣ ደመወዛችን ከአግባብ ውጭ የአንደኛ ዲግሪ እየተከፈልን ነው ሲሉ፣ አማርሮዋል።
እንደሚታወቀው የኢህአዴግ ስርዓት በቅርብ ግዜ የደመወዝ ጭማሬ በማድረግ የአስተማሪዎችን ኑሮ አሻሽያለሁ ሲል የሚደመጥ ሲሆን ፤ይሁን እንጂ ይህ አደረኩት ያለው የደመወዝ ጭማሪ፣ የመምህራንን ኑሮ በአግባቡ ሊያስተዳድር የማችል መሆኑን የተለያዩ  የሃገራችን መምህራን ምሬታቸውን እየገለፁ እንዳሉ ይታወቃል።   

No comments:

Post a Comment