Sunday, June 11, 2017

በዚህ ሳምንት የኢህአዴግ ስርዓትን በመቃወም በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ተቀላቀሉ፣



ከነዚሁ የተወሰኑ ስማቸዉ ለመጥቀስ
ወታደር መርዙ ጌቱ ከክልል 3 ሰሜን ሽዋ ዞን ሞረትናጅሩ ወረዳ የበደበጅ ቀበሌ ተወላጅ የ17ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጂመንት 1ኛ ሻምበል 2ኛ ጋንታ 1ኛ ቲም አባል የነበረ።
ወለገብሪኤል ተኽለማርያም  ከክልል 6 ኡሱስ ዞን 01 ወረዳ  ቀበሌ 01 ተወላጅ  
አድሓኖም ታደሰ ከክልል 1 ሴ,ምዕራብ ዞን ታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዓዲ ፀፀር ቀበሌ
ፍቓዱ ጎርፉ  ከክልል 1 ሴ,ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ ዓዲ ካሕሱ ቀበሌ
ማክቤል ታደሰ  ከክልል 1 ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑሞራ ወረዳ 04 ቀበሌ
ዝያዳ አማን ከክልል 4 አሩሲ ዞን ዴራ ወረዳ 02 ቀበሌ  
ሓዱሽ ንጉሰ ከክልል1 ማእከላዊ ዞን መረብለኸ ወረዳ ምሕቓን ቀበልየ
ተሽመ ኪሮስ  ከክልል 1 ማእከላዊ ዞን መረብ ለኽ ወረዳ ደብረሓርማዝ ቀበልየ
ታደሰ ተስፋይ  ከክልል 1 ምስራቃዊ ዞን ጋንታአፈሹም ወረዳ ዓዲግራት ከተማ ቀበሌ 06
ሲሆኑ እነዚህ ወጣቶች ወደ ትህዴን መጥተው እንዲታገሉ ያስገደዳቸውን ምክንያት በጋራ ሲገልፁ የኢህአዴግ ስርዓት በህዝባችን ላይ በሚጥለው አፈናና  በሃገራችን እያጋጠመ ባለው ስራ አጥነት ተማርረው እንደሆነ ገልፀዋል።
በተለይ ወጣት ወለገብርኤል ተኽለማርያም እንደገለፀው፤ የመላው ህዝብ አንድነት ፓርቲ አባል የነበረ ሲሆን በስርዓቱ ካድሬዎች ማስፈራራት ሆነ ግፍ ይደርስበት እንደነበረና በሌሎች ችግሮች ተማርሮ ለመታገል ወደ የትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል የተቀላቀለ መሆኑን ገልጿል።
ወታደር ብርዙ ጌታ በበኩሉ በማይፈፀም ኢህአዴግ ቃል ተታልሎ ወደ ውትድርና   እንደገባና በኋላ ግን ውትድርናው እድገትና ሞያ የሌለው እርስበርስ መገዳደል የበዛበት በመሆኑ  ወደ ትጥቅ ትግል እንደገባ ይገልጿል።
በመጨረሻም  ወጣቶቹ  በፀሎት የሚወድቅ ፀረ_ህዝብ ስርዓት ስለሌለ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ የወያኔ ኢህአዴግን ስርዓት ለመገሰስ እየተካሄደ ላለው  ሁለ ገብ ትግል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

No comments:

Post a Comment