Saturday, July 1, 2017

የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ሥራቸውን በፈቃዳቸው በሚለቁ ፖሊሶችና ሹመኞች በተፈጠረ ውዝግብ እየታመሰ ነው።



በተለይ ሰሞኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የአቶ ዓለምነው መኮነን አጃቢ በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል መገደላቸውን ተከትሎ እስከ ኮማንደር ድረስ ማዕረግ ያላቸው ፖሊሶችና አዛዦች በፈቃዳቸው ከሥራቸው እየለቀቁ ነው ተባለ።
የምዕራብ ጎጃም ዞን የምርመራ ሀኃፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ውስጥ በኮሚሽነር ደረጃ የልዩ ወንጀሎች ምርመራ ሀላፊ ሆኖ ሢሰራ የነበረው ኮማንደር በላይ ባለፈው  ዕለት በራሱ ፈቃድ ከሥራው መሰናበቱን አስታውቋል።
የልዩ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ኃላፊ የነበረው ኮማንደር በላይ፤ በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው ግምገማ ላይ “ይቅርብኝ ፣ አልፈልግም!” በማለት ሥራውን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን በግልጽ አስታውቋል።
ይህ እንዲህ እንዳለ፤ የክልሉ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁ ጠንካራ ትችቶችን ከሰነሰረ በኋላ “ዛሬ ላይ ማን ለማን እንደሚሰራ አይታወቅም፣ እኔም በዚህ ሁኔታ መሥራት አልችልም” በማለት ስራውን በፈቃደኝነቱ የለቀቀው ከ ቀናት በፊት ነበር።
ማን ለማን እንደሚሠራና እንደሚሰልል የማይታወቅበት ደረጃ ላይ በመድረሱም በክልሉ መስተዳድርም ሆነ በብአዴን ውስጥ የእርስበርስ መጠላለፉና መወነጃጀሉ ተባብሶ መቀጠሉ መረጃው በድጋሜ አስታዉቆዋል።

No comments:

Post a Comment