Sunday, December 17, 2017

ለዉጥ አልባ ተደጋጋሚ የህወሓት መግለጫ!



   የህወሓት ቡድን የህዝብ ልጆችን መስዋእትነትና መራራ ትግል ተንተርሶ የደርግን ኣምባገነን ስርዓት በመገርሰስ መንበረ ስልጣኑን ከተቆናጠጠ በኋላ ያሁሉ በበረሃ በነበረበት ጊዜ እየገባው የነበረ ቃላት በመክዳት ለጀግኖች ታጋዮችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደቆሻሻ በመጣል የአገራችን ሙሁራንና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያላመነበት ሕገ-መንግስት ብሎ በወረቀት በመጻፍ ለዘመናት አንድነትዋን ጠብቃ የኖረች አገራችን በክልሎች ከፋፍሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ለየራሱ እንዲራራቅና እንዲጣላ በማድረግ የዴሞክራሲ ጭላንጭል አጥፍቶ አገራችን የኪራይ ሰብሳቢዎችና የድህነት ማሳያ እንድትሆን አድርጓታል።
  ባሳልፍነው 27 ዓመታት የህወሓት ኢህአዴግ የስልጣን ዘመን በኢትዮጵያዊነትህ መኩራትና ማሰብ ቀርቶ መገዳደል፣ መለያየት፣በአይነ ቁራኛ መተያየት፣ልመና፣ስደት፣ፍትሕ መጓደልና በክልልህ ብሎም በአዉራጃህና በቀበሌህ ማሰብ ሰፍኖዋል። ሕወሓት ኢህአዴግ እስካሁን ድረስ አለም የደረስችበት ደረጃ መድረሱን ቀርቶ  ለኢትዮጵያ ጭቁን ህዝብ ከድህነት የሚያላቅቅ ፖሊሲ ሊከተል አልቻለም።
 ህወሓት ጭቁን የትግራይ ህዝብ በመጉዳት ካድሬዎቹ ከመጠን በላይ የሚጠቀሙበት ፖሊሲ ተከትሎ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ልዩ ተጠቃሚ በማስመሰል የደርግን ስርዓት እያስታወሰ እኔ ነኝ የሚሻለው ሕወሓት ከሌለ የትግራይ ህዝብ የለም የትግራይ ህዝብ መራራ መስዋእትነት የከፈለው በሕወሓት እንዲመራ ነው ካልሆነ የባሰ ችግር ይፈጠራል እያለ ነጋ ጠባ የትግራይ ህዝብ ሲያስፈራራ ይታያል።
 እርግጥ ነው በአገራችን አሁን ባለው የሕወሓት ኢህአዴግ ስርዓት በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች የትግራይ ተወላጆች አሉ። የትግራይ ተወላጆች ሆነው ለአገርና ለህዝብ የሚበጅ ደህና ስራ ቢሰሩ ባይጠላ ነበር። ነግር ግን በስመ ትግራይ ህዝብ እየነገዱ አገርን እያጋጩ ኢ-ሰብአዊና ኢ-ዴሞክራስያዊ ትግባራት ሲፈጽሙ ነው የምናየው።
  ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባርና ተንኮል ደግሞ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ተረድቶና መርምሮ ጠላቱን ለይቶ መምታት እንዳለበት እንመክራለን። ምክንያቱ ሕወሓት የስልጣኑን ዕድሜዉን  ለመራዘም የማይፈጥረው ተንኮልና የማፈንቅለው ድንጋይ ስለሌለ።
 መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሕወሓት ወደ ሚፈልገው የጥፋት ጓዳና በሚገባ ተረድቶ ማንንም ቢሄር ከሌሎች ብሄሮች ለይቶ ሳያይ  በአንድነት በመነሳት የሕወሓት ስርዓት አታስፈልገንም ሌላ ህዝብ የመረጠው ዴሞክራስያዊ ስርዓት ይንገስ በማለት ዴሞክራስያዊ ትግሉን እያደረገው እንደሚገኝ በሰለጠነ መንገድ መቀጣጠል ይገበዋል።
  ሕወሓት ህዝብን ለማደናገር በየጊዜው በሚያወጣቸው መግለጫዎች ይታወቃል። በዚህ ሳምንትም የተለመደው የመደናገርያ መግለጫዉን ራሱ በሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች ሲያሰማ ቆይተዋል።መግለጫው ከህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ የተሰጠ ሲሆን ያለው ዴሞክራስያዊ ስርዓት ገምግመን ያሉን መሰረታዊ ድክመቶች በዝርዝር ፈትሸናል የሚል ሲሆን የተጠቀሱት ድክመታችን ደግሞ የሚከተሉት ናቸው ይላል።
 በትግል የተመረኮሰው ማእከላይ ኮሚቴ እንድነት እንደሌለው፣ በመጠቃቃትና በመቻቻል የተመሰረተ ዝምድና እንደነበረው፣ጸረ ዴሞክራሲ ተግባሮች እንዳሉት፣  የአዲሱ ትዉልድና የተማረው ሕብረተሰብ በመጠቀምና በመግንባት ሂደት ትልቅ ጉድለት እንዳለው። የትግል አጋር ከሆኑ ድርጅቶች የነበረው ግንኙነት ችግር እንድነበረው፣  በትምክህተኞችና ጠባብ ሃይሎች በአገራችን የተፈጠረው አደጋ፣ በትግራይ ክልል የልማት ሂደት የአስተዳደር ችግር መኖሩን  በትኩረት ገምግመናል የሚል ነው። ለተጠቀሰዉን ችግር ምክንያት የሆነው ደግሞ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን በመግለጫው አምነዋል የሕወሓት ማእኸላይ ኮሚቴ።
  ሕወሓት ከባህር በጭልፋ ችግሮቹን ማመኑ አንድ ነገር ሆኖ ለምን ችግሮችን እየፈጠረ ችግሮችን በመድገም ተሳስተናል የሚል መግለጫ  በአዞ ለቅሶ  ከሚደጋግም ካለፈው ስህተቱ ተምሮ የጭቁን ህዝብ ሩሮ የሚያሻሽልና አገርን የሚያስታርቅ መልካም ስራ አይሰራም? ወይም የያዝኩት ስልጣን ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ስልጣኑን ለህዝብ አያስረክብም? ይህ ሕወሓት የሰጠው የተለመደው የመደናገርያ መግለጫ በስርዓቱ መዋቅር ላይ የተሻሻለ መንገድ እንዲከተል ሳይሆን እሁንም አደናግሮ የስልጣኑን ዕድሜ ለማራዘም ስለ ሆነ ለዉጥ አልባ ተደጋጋሚ የህወሓት መግለጫ ብለን ጠቅሰነዋል።
 

No comments:

Post a Comment