Monday, February 19, 2018

ጭቆና ያማረረው ህዝብ በረጋጮች ጥገና አይገዛም



 ይህ የሰማእታቱ አደራ፤ጧሪ የሌላቸው የስውዓት ቤተሰቦችና አካላቸውን ያጡ ታጋይ ጓዶቹን በአጠቃላይ ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ከእጅ ወደ አፍ በሆነ አኗኗር፣ ኑሮውን የሚመራውን ህዝብ ከድቶ ግላዊ ህይዎቱንና የስልጣን እድሜውን የሚያደላድልለትን ቦታ እያመቻቸ የመጣ የህወሃት ቡድንና ካድሬዎቹ አመት በመጣ ቁጥር በህዝቦች ትግል ሲያላግጥ ይታያል።   
   እነዚህ በየአመቱ እንደ ፕሮፖጋንዳዊ ፍላጎት ማሟያ የሚጠቀምባቸው መድረኮች የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል አንዱ በስውኣትና የስውአት ቤተሰቦች እየማለ የሚያስታውስበት የሰማእታት ቀን ሲሆን ሌለኛው ደግሞ የካቲት 11 ተጀምሮ የድሉ ፍሬም ለጥቂቶች እንዲያገለግል የተደረገ የትግራይ ህዝብ ትግል ልደት የሚመለከት ነው።
    እርግጥ ነው የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ ትግል ጥቂቶች ጀምረውት ሺዎች እንዲከተሉት እና እንዲሰባሰቡበት ከዚህ ባለፈም ከትንሽ ንብረቱ እስከ ክቡር ህይወቱ ሁሉም ህዝብ አለሁ እራሴ እያለ የማይተካ ሚና ተጫውቷል። ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል።  
    ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ተደራራቢ ግፍና በደል እየደረሰበት በአሸናፊ ትግሉ ሲያሳልፈው፣ ለዘመናት ለራቀው የተረጋጋ ሰላም እንደገና ሲያጣው፤ የትግሉ ውጤትና መስዋዕቱ ለጥቂቶች ብልጦች መቀለጃ ሲውል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ሲታፈን፤ ተጠቃሚነቱ እርቆት በአጠቃላይ በማይተካ ህይዎቱና የልጆቹ ህይወት ገብሮ ያቆመው ስርዓት ተመልሶ ሲረግጠውና በላዩ ላይ ሊቀልድ አይደለም ነበር።
   በተመሳሳይም በማንኛውም የአገሪቱ አካባቢ ተንቀሳቅሶ እንዲሰራና ተቻችሎ እንዲኖርና እንዲሰፍር እንጂ እንዲዚህ እንደ አሁኑ ሃገሩ መመቻውና መባረሪያው ትሆናለች የሚል ስጋትም ይሁን ጥርጣሬ አልነበረውም።
    ሆኖም ግን የህዝቦችን ትግል በመስረቅ ለአምባገነንነትና እኩይ ተግባራት የተሰማራው ገዥው የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት በአጠቃላይ በተለየ ደግሞ የህወሃት አመራሮች እየተከተለው የመጣ የውድመት መንገዶች በአደጋ ተከቧል።
    ህወሃት በንብረቱና በህይወቱ አይከፍሉት ከፍሎ ለወንበር ያበቃውን ህዝብ ከድቷል ብቻም ሳይሆን በጠባብ አንኬል ሊታጠርና በራሱ ስብከትና አምልኮ ተገድቦ እንዲጓዝ የሚያስችል መንገዶች እየተከተለ በመምጣቱ በየቀኑ የምናየውና እየሰማነው ያለነውን አደጋ አውርዶበታል። 
   ይህ ተፈጥሮ ያለው አደጋ የአንድ ወቅት ክስተት ሳይሆን የህወሃት አመራር በየወቅቱ ሲከተለው የመጣ አውዳሚ ተግባራት ለማረም ከህዝብ የሚቀርብለትን ምክርና ነቀፌታ ጀሮ ዳባ ልበሽ በማለት ወደ ስርቆትና አምባገነናዊነት እየተሰማራ ችግሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲባባስ እያደረገ መጥቷል ብቻም ሳይሆን ቡድኑ እርስ በራሱ መዋቅር እየፈጠረ ሃገር ወደ ኋላቀር፤ድህነትና፤ የመበታተን አደጋ እንዳጋለጠ ራሱም እየሰጣቸው ባሉት መግለጫዎቹና ግምገማዎቹ መስማትና ማየት ይቻላል።   
  ይህ ቡድን ተከስቶ ባለው አገራዊ ነውጥና አለመረጋጋት እርስ በርሱ እንደዓሣ ለመበላላት በደረሰበት ጊዜ ደግሞ ከሁለት አመታት በፊት በተቀናቃኞቹ ተቀምቶ በአዲስ አበባ ተሰማርቶ የቆየ ቡድን ስኬታማ ሊያደርገው የሚችል ፈጠራዎችና ኔት ወርክ ሲያጠናክር ከቆየ በኋላ በተፎካካሪዎቹ ድል በማስመዝገብ የጥቂቶችን ሹመትና የቢሮ ሃላፊዎችን እንዲሁም ካድሬዎችን እንዲወርዱና እንዲጠነቀቁ በማድረግ የተወሰነ ጥገናዊ ለውጥ በማድረግ ወደ ለመደው የክህደት መንገድና ውድመት እያወረደ በመምራት የተለያየ ንስሃና ፀፀት ያሰማል።
   “ጅብ እስከሚነክስ ያነክስ” እንደተባለው ለሩብ ዘመን ሲከተለው የመጣውን አውዳሚ ተግባሮች ዛሬ ላይ ደርሶ ተግባራዊነት በሌላቸው የቁጥር ስህተቶችና በህዝብ ላይ በሚደርሱ በደሎች ብጣሽ ወረቀት አድርጎ መግለጫና ተማፅኖ በሚዲያ በማቅረቡ የሚያመጣው ተኣምር የለም።
እንዲያውም የስርዓት ለውጥ ለማምጣት የተነሳን የመላ የአገራችን ህዝብ ትግል በረጋጮች እና ከሃዲዎች ጥገና የሚድን ችግር ስለሌለ፣ ዛሬ የህዝብ እንቢተኝነት ከፍ ባለና በተቀጣጠለ ደረጃ ደርሶ ስላለ ህወሃት ለብቻው የሚፈታው የህዝብም ይሁን የሃገር ችግር የለም።

No comments:

Post a Comment