አሁን እየተወሰደ ያለ እርምጃ በህዳር ወር 2005 ዓ/ም የኢህአደግ መንግስት ስለ ግብር አከፋፈል ስርዓት
በተመለከት የከተማዋን ነጋዴዎችን ለማነጋገር በሰበሰበበት ወቅት መንግስት
የወሰነውን ግብር መክፈል ያልቻለ ማንኛውም ነጋዴ የንግድ ድርጅቱ ታሽጎ የንግድ ፈቃዱ እንደሚነጠቅ ሃላፊነት የጎደለው ማስጠንቀቅያ
የሰጠ ሲሆን አሁን እየተወሰደ ያለ እርምጃም ውሳኔውን ተከትሎ የመጣ ሆኖ ፥ ድርጊቱ ስርዓቱ በውድቀት አፋፍ ላይ መሆኑን የሚያመላክት
ነው ሲሉ አንዳንድ ወገኖች ይጋገራሉ።
በደረሰን ዘገባ መሰረት በውዲ ሴሮ የሚታወቅ በከተማዋ የህንፃ መሳሪያዎች መሸጫና ማከፋፈያ የንግድ ድርጅት
1.3 ሚልዮን ብር፤ አቶ አስማረ አረጋይ የህንፃ መሳሪያዎች መሸጫ የንግድ ድርጅት ባለቤት 500 ሺ ብር ፤ እንደዚሁም አቶ ገብራይ
የተባለ ነጋዴ 260 ሺ ብር ግብር እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው ሲሆን ነጋዴዎቹ የተጠየቁትን ግብር ከአቅማቸው በላይ ሆኖ መክፈል ስላልቻሉ
መንግስት የንግድ ድርጅቶቻቸውን በማሸግ የንግድ ፈቃዳቸውን መንጠቁን ለማወቅ ተችለዋል።