Monday, March 28, 2016

የመቀሌ የባጃጅ በለ ዋና ማሕበር ለከተማዋ አስተዳደር በመቃወም ስራ የማቆም አድማ አካሄዱ።



ምንጮቻችን ከከተማዋ አንደጠቆሙት በመቀሌ ከተማ የባጃጅ በለ ዋና ማሕበር የሆኑት ባለሃብቶች አስተዳደሩ ያወጣው ቅጡ የጠፋው የባጃጅ ህግ በመቃወም ከመጋቢት 14 /2008 ዓ.ም ጀምሮ በቀበሌ 13 አከባቢ የሚገኝ የማህበሩ  ፅፈት ቤት የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል።
   የተቃዉሞው ዋናኛ ምክንያት ደግሞ የከተማዋ የትራንስፖርት ፅፈት ቤትና አገልግሎት የባጃጅ ባለ ዋናዎች ከ መጋቢት 1 /2008 ዓ.ም ጀምረው ከተመደበላቸው ዉጭ በማለፍ ወደ ሌላ ቦታ የኩንትራት አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉና የሚንቀሳቀሱበት ቦታ ደግሞ ታፔላ እንዲደረግበት የሚል ሆኖ ለዚህ በመቃወም ደግሞ ማህበሩ በሙሉ ድምፅ ስራ የማቆም እርምጃ እንዲወስድ ወስኖ በመቃወሙ መንግስት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ከተገልጋይ ህዝብ ብዙ መሰረታዊ ጥያቄዎች ስለቀረበበት የባጃጁ መስመር በትላልቅ ታክሲዎች እንደተካው ለማወቅ ተችለዋል።
  የባጃጅ ባለዋናዎች በመንግስት እንዲንቀሳቀሱ የተወሰነላቸው የመቀሌ አከባቢዎች ለመጥቀስ የሚቻል ሓዉዜን አደባባይ መቀሌ ሆስፒታል፤ እንዳዓኾራ፤ ዕላላ፤ ጅብሩኽ፤ 17 ቀበሌ፤ ጅብሩኽ-18 ቀበሌ ላሌም የሚል ሆኖ፣ መንግስት ይሄንን ለማድረግ ለ6 ወር አከባቢ ሲዘጋጅበት የቆየ መሆኑ ከገለፀ በኋላ በተለይ ከአድማዉ በኋላ ባጃጆቹ ማታ ማታ የሚሰሩት የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያቋርጥ እንደተደረገ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment