ከአላማጣ ከተማ ኗሪ ህዝብ በመንጠቅ ለባለሃብቶች እየተሸጠ ያለው መሬት የሃገሪቱን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌን
የጣሰ ነው ፣ መሬት አይሸጥም አይለወጥም የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ እየተፈጸመ ያለው ተግባር የኢህአደግ ስርዓት ቆሜሌታለሁ
ለሚለው ህገ-መንግስትም ተገዥ አለመሆኑን የሚያመለክት ነው ሲሉ የከተማዋ ኗሪዎች ይገልጻሉ፣
የኢህአደግ ስርዓት ባለስልጣናት መሬትን እንዳሻቸው እየቸበቸቡ ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ ስለህዝብ ሆነ ስለ
ሃገር ቁብ እንደሌላቸው በራሳቸው ላይ ደርሶ የተመለከቱ የከተማዋ ኗሪዎች መሬት ከህዝብ እየነጠቁ የመሸጥ ተግባርን በመቃወም ህገ-መንግስቱ
ይከበር ፤ ቅድሚያ ለህዝብ ህልውና እንዲሰጥ ፤ ዜጎች በሃገራቸው በሰላም የመኖር መብታቸው ይጠበቅ የሚሉ ጥያቄዎችን በመያዝ የተቃወሞ
ሰልፍ ማድረጋቸውን ቷውቋል ፣