Friday, March 22, 2013

ኗሪነታቸው በአማራ ክልል ፤ በምእራብ ጎጃም ዞን ፤ በፍኖተ ሰላም የሆኑ 4 ወጣቶች መጋቢት 5/2005 ዓ/ም በፌደራል ፖሊስ ታፍነው መወሰዳቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ወጣቶቹ ከጓደኞቻቸው ጋር ሆነው በአንድ በከተማው በሚገኝ ሻይ ቤት ውስጥ ተሰባስበው በመጫወት ላይ በነበሩበት ወቅት በወጣቶቹ አንድ ላይ መሰባሰብ ደስተኛ ያልሆኑ የስርዓቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከወጣቶቹ መካከል አራቱን ወጣቶች በጸጉረ ለወጥ ስም አፍነው በመውሰድ እሰር ቤት የከተቷቸው ሲሁን ቀሪዎቹን አስፈራርተው እንደለቀቋቸው ለማወቅ ተችለዋል፣
የኢህአዴግ መንግስት በፍኖተ ሰላም ከተማ ኗሪ ህዝብ በተለይም የወጣቱ እንቅስቃሴ እያሰጋው በመምጣቱ ወጣቱን ከወዲሁ ለመቆጣጠር ሲል በከተማዋ ባሰማራቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ንጹሃን ዜጎችን ማሰርና ማዋከብ እለታዊ ተግባሩ እየሆነ መምጣቱን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣