Friday, March 22, 2013

በአ/አ ከተማ ፤ ቦሌ ክ/ከተማ በኮብል ስቶን ስራ የተሰማሩ የደቡብ ክልል ተወላጆችና በብሄረ ኦሮሞ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ቷውቋል፣



የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ከሆነ የግጭቱ ዋና መንስኤ የኢህአዴግ ስርዓት በሚከተለው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሆኖ ፤ የደቡብ ክልል ተወላጆች ግዜው የኛ ነው በማለት በብሄረ ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጫና ለማድረግ በመሞከራቸውና ግጭቱ በህብረተሰቡ ውስጥ ዘልቆ በመግባቱ ወደ ብሄር ግጭት ተለውጦ ከመጋቢት 4/2005 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ቀጥሎ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችለዋል፣
በግጭቱ ምክንያት ከሁለቱ ብሄር ተወላጆች 26 ሰዎች የሞቱ ሲሆን የብሄረ ኦሮሞ የሚገኙባቸው በርካታ ወጣቶች ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፣ ግጭቱ እስካሁን ድረስ እንዳልበረደ ቷውቃል፣
የኢህአዴግ መንግስት በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት ህዝቡን በተለይም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎች ከሞያቸው ጋር በማይሄድ በኮብለስቶን ስራ ተሰማርተው በመስራት ላይ ከሚገኙ ወጣቶች ሊመጣበት የሚችል ተቋውሞ በመስጋት ወጣቶችን በብሄር በመከፋፈልና በመካከላቸው ግጭት በመፍጠር እድሜው ለማራዘም እንደ አንድ ዘዴ እየተጠቀመበት መሆኑ ዘገባው ጨምሮ ያስረዳል፣