በመቐለ ዞን የኲሓ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባላት ጥቅምት 7,2006 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ የ
2005 የበጅት ዓመት አፈጻጸም በመገምገም የ 2006 ዓ/ም በጀት ለማጽደቅ በሚል አጀንዳ የተያዘ ቢሆንም ተሰብሳቢዎቹ በክ/ከተማዋ
በሙስና የተጨማለቁ አስፈጻሚ አካላት ከሃላፊነታቸው ሳይነሱ የምናጸድቀው በጀት የለም ሲሉ በአንድ ድምጽ መቃወማቸው ቷውቋል፣
የምክር ቤቱ አባላት ባቀረቡት የመቃወሚያ ሃሳብ ባለፈው የበጀት ዓመት አብዛኛውን በጀት በስራ አስፈጻሚው
አካል መጠፋፋቱን በግምገማ ተረጋግጦ ሲያበቃ እስካሁን ድረስ ወንጀሎኞቹ ወደ ህግ አልቀረቡም ክስ አልተመሰረተባቸውም ከሃላፊነታቸው
ሳይነሱ እንደ ብቁ አመራር ተቆጥረው በስራቸው እንዲቀጥሉ ለምን ተደረገ በቂ ምላሽ አልተሰጠንም ስላላመንበት የ 2006 ዓ/ም በጀት
በሃላፊነት አናጸድቅም በማለት አጀንዳውን ውድቅ አድርገውታል፣
ከሁለት ዓመታት በፊት ጀምሮ በክ/ከተማዋ አስፈጻሚ አካላት የሚፈጸመውን ሙስና መፍትሄ እንዲደረግለት በተደጋጋሚ
ሲጠይቁ ቢቆዩም በቂ ምላሽ ባለማግኘታቸው ቅር የተሰኙ የምክር ቤቱ አባላት የስራ አስፈጻሚው አካል ውሳኔአችንን አያከብርም ይህ
አካሄድ አሁንም መስተካከል አለበት በማለት ፊት ለፊት ከተከራከሩት የምክር ቤት አባላት መካከል።- ቄስ ገ/እግዚአብሄር አርአያ
፤ወ/ሮ ሓዳስ አስገዶም ፤ አቶ ሓጎስ ገ/ዋህድና አቶ ካሕሱ መለስ ይገኙባቸዋል፣