Friday, May 27, 2016

በሃረማያ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ እየተደበደቡና እየተቀጠቀጡ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።



በሃረማያ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች  የመብት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ  የፌደራል ፖሊስ  በተማሪዎች ላይ ከባድ ድብደባ በመፈፀም ጉዳት እያደረሱባቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው፣የሃረሚያ ዩነቨርስቲ ተማሪዎች   ቀጣይና የማያቋርጥ ተቃውሞ በማካሄድ ላይ ሲሆኑ ፣ በተመሳሳይ  በ ግንቦት 16 ቀን   2008 ዓ/ም  ሰለማዊ የመብት ጥያቄ  ባነሱ ተማሪዎች ላይ  ፖሊሶቹ  በየመኝታ ክፍሎቻቸው  በመግባት  እንደደበደቡዋቸውና ከባድ ጉዳት እንዳደረሱባቸውም ለማወቅ ተችሏል።
    ፖሊሶቹ ባደሩሱት ግፍ ቁጥራቸው እጅግ በርከት ያሉ ተማሪዎች የተደበደቡ ሲሆን ፣ቁጥራቸው ከ15 የማያንሱ  ተማሪዎች  ደግሞ በከባድ መጎዳታቸውን  የጠቀሰው መረጃው ፣ ተማሪዎችም ከመኝታ ክፍሎቻችው  እንዳይወጡ የህንፃው  ዙርያ በፌደራል  ፖሊስ በመከበቡ  ሊያመልጡ በሞኮሩበት ጊዜ  ደግሞ ፣ አንድ  ፌደራል ፖሊስ  ገፍትረው በመጣል ጉዳት እንዳደረሱበት ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment