በደረሰን ዘገባ መሰረት በመተማ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ሱዳን አሻግራችሃል በሚል በርካታ
ዜጎች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው በከተማዋ በሚገኘው እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ናቸው ፣ ያለ ማንም ማስረጃ በእስርቤት ተወርውረው
እየተሰቃዩ ካሉት ዜጎች መካከል አቶ ሽሻይ ገብረስላሰ ፤ አቶ ሞገስ ፍስሃ ፤ አቶ አስረስ ባይሳና ሌሎችም የሚገኙባቸው ሲሆን በደረሰባቸው
ድብደባ አካላቸው የተጎዱ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣
ቀደም ሲል በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ሲሻገሩ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት 4 ዜጎች ሲገደሎ
ሌሎች 6 ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የሚታወስ ነው፣